ፍትሃዊ የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ የተማሪ ቅበላን 1,253,737(106%) ማድረስ ተችሏል፤
ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር አፈፃፀሙ ሲነፃፀር 89,049 ብልጫ ያለዉ ነዉ፡፡
የትምህርት ፍትሀዊነትን ከማስፈንም አካያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎች ቁጥር 33,672(100%) ማድረስ ተችሏል።
በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በተሰራዉ ስራ በገንዘብ 3,841,682,948.15፣ በዓይነት 137,566,563.36፣ በጉልበት 19,800,640.85 እና በእውቀት 26,380,054.45 በድምሩ ብር 4,025,430,206.81 በመሰብሰብ የትምህርት ግብዓትን ማሟላት ተችሏል፡፡
በዘላቂነት የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ግብዓትን ከማቅረብ አንፃርም ለ1,037,500 (100%) ተማሪዎች ዩኒፎርም፤ለ9,125,435 (100%) ተማሮዎች ደብተር በማሰራጨት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
በተማሪ ምገባ አገልግሎት 835,069 (100%) ተማሪዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ የተቻለ ሲሆን የተማሪ የቅበላ አቅም ለማሻሻልና የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋጋጥ የተሰራው ስራ አበረታች ዉጤት አምጥቷል፡፡
በከተማችን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ተገቢነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ በ126 ተቋማት ላይ የውጭ ኢንስፔክሽን በማካሄድ የደረጃ ምደባ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች ተደራሽ ተደርጓል።
ለትምህርትና ስልጠና የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ጥያቄ ላቀረቡ 660 (94.7%) ተቋማት የእውቅና እና የእድሳት ተሰጥቷል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
