ከንቲባ አዳነች አቤቤ የነዋሪዎችን የኑሮ ጫናን ለማቃለል የተዘረጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተመለከተ፦
– በበጀት አመቱ አጋማሽ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በሚከናወኑ የሰው ተኮርና የበጎ ፈቃድ ተግባራት 1,197,413 (ከ100% በላይ) የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
– በዚሁ መሰረት 24 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመክፈት በየቀኑ በአማካይ እስከ 36,000 ለሚደርሱ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ለማግኘት የሚቸገሩ ነዋሪዎቻችንን እየመገብን ነው፡፡
– ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያን፣ ለሀገር ባለውለታዎችና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች 3,737(74%) ቤቶችን በመገንባት 20,484 (77%) ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
– ለ917,829 (ከ100% በላይ) በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራት ተችሏል። በህብረተሰብ ተሳትፎ ለሚሰሩ መሰረተ ልማት ስራዎች ብር 479,361,717.8 እንዲሁም በበጎ ፈቃድ 8,714,683,077 በድምሩ ብር 9,194,044,794.80 ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል።
