+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

 አደረጃጀት

መንገድ ሀብት

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጠን በተለያዩ የመዲናዋ አካባቢዎች የመንገድ ሀብቱን በሚገባ ለመከታተልና ለመጠበቅ የሚያስችል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች እንዳሉት ይታወቃል፡፡የተቋቋሙት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በዋናነት የህብተሰቡን የመንገድ አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረጉ ቢሆንም ስለ መንገድ ሀብት ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ በመንገድ ሀብት እየደረሱ ያሉ ጥሰቶችን በቅርበት መከታታልና አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እየሰጡ ይገኛል፡፡በተጨማሪም ጉዳት ባደረሱ አካላት ላይ ከተለያዩ ከባለ ድርሻዎች ጋር በጋራ በመሆን እርምጃ የመውሰድ ተግባርም ያከናውናሉ፡፡

በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች እና መገኛ ቦታቸው፡-

  1. ምስራቅ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር

መገናኛ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል አጠገብ ህብር ወርቅ ህንፃ 8ኛ ፎቅ

ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ቦሌ ክፍለ ከተማን ማዕከል አድርጎ የተቋቋመ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ማንኛውም መንገድ ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ ከቅርንጫፍ  ፅ/ቤቱ መረጃ ማግኘትና መገልገል ይችላል

ስ.ቁ፡- 011-878-71-39/76

  • ምዕራብ አ/አ መንገድ ሀብት አስተዳደር

ጦርሀይሎች 3 ቁጥር ማዞሪያ መንገድ በቀለ እሸቴ ህንፃ 6ኛ ፎቅ

ኮልፌ እና አዲስ ከተማን ማእከል አድርጎ የተቋቋመ በመሆኑ በሁለቱ ክፍለ ከተሞች የምትገኙ ነዋሪዎች ማንኛውም መንገድን የተመለከተ መረጃ እና አገልግሎት ማግኘት ትችላላችሁ

ስ.ቁ፡-011-872-29-89 ወይም 011-878-71-55

  • ሰሜን አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር

ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የካ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞችን ማእከል አድርጎ የተቋቋመ ሲሆን ሰሜን ማዘጋጃ ጉለሌ ውልና ማስረጃ  ፅ/ቤት ካለበት ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል

በጉለሌ እና በየካ ክፍለ ከተማ የምትገኙ ነዋሪዎች ማንኛውም መንገድ ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ ከቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ መረጃ ማግኘትና መገልገል ትችላላችሁ

ስ.ቁ፡-011-878-71-32/33/34

  • ደቡብ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር

አቃቂ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞችን ማእከል ተደርጎ የተቋቋመዉ  ፅ/ቤት መከኒሳ ሲዶ ህንፃ ላይ ይገኛል፡፡ በነዚህ ክፍለ ከተሞች የምትገኙ የመዲናዋ ነዋሪዎች ማንኛውም መንገድ ነክ ጉዳዮች በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በኩል መረጃ ማግኘትና መገልገል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

ስ.ቁ፡-011-878-71-50/19/35

  • ማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር

የአራዳ፣ ቂርቆስ እና ልደታ ክፍለ ከተሞችን ማዕከል ተድርጎ የተቋቋመው የማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ቢሮ አፍንጮ በር አደባባይ በሚገኘው ፍቅር ፕላዛ ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በነዚህ ክፍለ ከተሞች የምትገኙ የመዲናዋ ነዋሪዎች ማንኛውም መንገድ ነክ ጉዳዮችን በቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በኩል መረጃ ማግኘትና መገልገል የምትችሉ መሆኑን በድጋሜ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ስ.ቁ፡-011-878-71-47/25