ተግባርና ኃላፊነት
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጠን በተለያዩ የመዲናዋ አካባቢዎች የመንገድ ሀብቱን በሚገባ ለመከታተልና ለመጠበቅ የሚያስችል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች እንዳሉት ይታወቃል፡፡የተቋቋሙት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በዋናነት የህብተሰቡን የመንገድ አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረጉ ቢሆንም ስለ መንገድ ሀብት ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ በመንገድ ሀብት እየደረሱ ያሉ ጥሰቶችን በቅርበት መከታታልና አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እየሰጡ ይገኛል፡፡በተጨማሪም ጉዳት ባደረሱ አካላት ላይ ከተለያዩ ከባለ ድርሻዎች ጋር በጋራ በመሆን እርምጃ የመውሰድ ተግባርም ያከናውናሉ፡፡