+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በካፒታል ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደረግናቸው የልማት ስራዎች

በካፒታል ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደረግናቸው የልማት ስራዎች ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጡ ፤የገቢ ምጭን የሚያሳድጉና ወጪ የሚቀንሱ ናቸው::የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ

በካፒታል ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደረግናቸው የልማት ስራዎች ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጡ ፤የገቢ ምጭን የሚያሳድጉና ወጪ በሚቀንሱ ሁኔታ የተገነቡት ከ15.960 በላይ ፕሮጀክቶትን ህብረተሰቡ ትብብር፤ በባለሀብቶች ድጋፍና በመንግስት ወጪ ማሳካት የተቻለነው ብለዋል፡፡

ከ2010 ጀምሮ እያደገ የመጣውን የከተማዋን የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በማሳድ፤የግንዛቤ ስራ በመስራትና አዳዲስ የገቢ መሰረት በማስፋት ገቢን ማሳደግ ተችሏል፡፡

የሴቶችን የአመራር ሰጪነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ በአመራር ሰጪነት ከ33% በላይ ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፤ በማህበራዊ ፤ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየስራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን በማስፋት በተለይም በከተማዋ በስፋት የሚስተዋለውን የትራፊክ ማኔጅመንት ላይ የሚነሱ ክፍተቶችንና የፓርክንግ አገልግሎት ችግር ለመቅረፍ በኮሪደር ልማት ስራችን የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

ማህበራት ላይ የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ፤ ሪፎርም በማድረግ፤ በማዘመንና አቅማቸውን በማሳደግ ወደ ኢንቨስትመንት እንዲደገቡ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው፡፡

ከንግድ ስርዓት ጋር በተያያዘ ሰፋፊ ስራዎችን አቅርቦትን በማይጎዳ መልኩ የቁጥጥር ስርዓቱን በማስፋት ከ36.000 በላይ ህገ-ወጦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ወደ መደበኛ ስርዓት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

የፍሳሽ ማስወገድ ስርዓት በማዘመን ወደ ወንዞች የሚፈሱ ፍሳሾችን ለማስወገድና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንዲያስችል በኮሪደር ልማቱ ሰፋፊ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Comments are closed.