+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የጠሮ ሥላሴ አካባቢ የመንገድ እድሳት

“የረጅም ጊዜ ችግራችን መፍትሄ አግኝቷል” የአካባቢው ነዋሪዎች

የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን፤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ጠሮ ሥላሴ ልዩ ስሙ ሹራብ ማህበር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በመልሶ ግንባታ ደረጃ በማደስ ላይ ይገኛል።

የምዕራብ መንገድ ጥገና ኘሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ያሬድ ተከተል፤ በአካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው መንገድ በመቆፋፈሩ ምክንያት ለትራፊክ እንቅስታሴ ምቹ እንዳልነበር ጠቅሰው፤ አሁን ላይ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የጥገና ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ኢንጂነር ያሬድ፤ የመንገዱ መጠገን ከአስኮ እና አዲስ ሰፈር የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ወደ 18 እና አጠና ተራ ቀለበት መንገድ በአጭር ርቀት ለማቋረጥ የሚያገለግል ከመሆኑም ባሻገር ዊንጌት አደባባይ ላይ የሚኖረውን የትራፊክ መጨናነቅ እንደሚቀንስ ገልፀዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ቻለው ኢላላ እንደገለፁት፤ መንገዱ በመበላሸቱ ምክንያት ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለነዋሪዎች ጥያቄ ምላሽ በመስጠቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ አቶ መንግስቴ በበኩላቸው፤ የመንገዱ መጎዳት በህብረተሰቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን አስታውሰው፤ አሁን ላይ የመንገድ ጥገና ስራ መጀመሩ የነዋሪውን ችግር በተፍተኛ ደረጃ የሚፈታ ነው ብለዋል፡፡

Comments are closed.