+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማችን እየተመዘገበ ያለው ውጤት አዲስ አበባ ደረጃዋን በሚመጥን የእድገት ደረጃ ውስጥ ያለች መሆኑን የሚያመላክት ነው

በከተማችን እየተመዘገበ ያለው ውጤት አዲስ አበባ ደረጃዋን በሚመጥን የእድገት ደረጃ ውስጥ ያለች መሆኑን የሚያመላክት ነው ፡፡ አቶ ሞገስ ባልቻ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ

የዚህ ስኬት ዋናው ሚስጥር ህዝቡ ለገዥው ፓርቲና ለአመራሩ ያሳደረው አመኔታ ለመመለስ የሚያስችል የአመራር የቁርጠኝነትና ምላሽ ሰጪነት ውጤት ነው፡፡

ይሄ በአገራችን የመንግስት አስተዳደር ሁኔታ የመንግስት ስልጣን የያዘ አካል ህዝብን ወደ ተሻለ ደረጃ ከማድረስ ጋር የነበረውን ጉድለት በከፍተኛ ሁኔታ ደረጃውን የሚያሻሽል እና ስታንዳርድ ሴት የሚያደርግ ህዝብን የማገልገልና የሚጠቅም ትልቅ ሪከርድ የሚስመዝገብ የአመራር ቁርጠኝነት ውጤት ነው፡፡የዚህ ቁርጠኝነት ምክንያትም ራእዩ ነው፡፡

አገርንና ከተማን ከመውደድና ከመለወጥ እንዲሁም ህዝብን ከመጥቀም ትልቅ ራእይ የሚመነጭ የአመራር የእለት ተለት ትጋት ውጤት ነው፡፡ ይህን በማድረጋችን አዲስ አበባ የልምድ መቅሰሚያ ማእከል እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ይህ ውጤት በጣም አበረታችና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ቢሆንም ከራእያችን አንጻር ገና የሚቀረን ነገር አለ፡፡

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እናደርጋለን ስንል እየጎለበተ ያለውን የህዝብና የአመራር ተግባርን ተቀናጅቶ የመፈጸም አቅምና ተግባርን በውጤት የማጀብ ብቃት በስፋት መጠቀም ይጠበቅብናል፡፡ የአመራራችን ተወዳዳሪ መሆንና አምሽቶ የመስራት የመፈጸም አቅም ከበፊቱ ባደገ መጠን መዳበር ይኖርበታል፡፡

የሴቶች ጉዳይ በአዲስ አበባ ነባራዊ ሁኔታ የለውጡ ከፍተኛ ትሩፋት የሆነና ከተሳትፎም በላይ በተለያዩ እርከኖች በአመራርነት ከፍተኛ እመርታ ለመፍጠርና ውጤት ለማስመዝገብ ያስቻለን ነው፡፡ በትምህርትና በፐብሊክ ሰርቪስ ከፍተኛውን ቁጥር የሚሸፍነው የሴቶች ቁጥር ነው፡፡

የወንዝዳር ልማትን በተመለከተ የከተማችንን ገጽታ ከመሰረቱ ሊቀይርና እመርታዊ ለውጥ ማስመዝገብ የሚያስችል እንዲሁም በወንዞች ላይ ያለንን ግንዛቤና አጠቃቀም ከመሰረቱ የሚቀይር ግዙፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው ተግባር ነው፡፡

በመጨረሻም ከተማችንን ጽዱና ውብ የማድረግ ስራችንን ለማሳካት ህዝቡ የተለመደውን ትብብሩን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Comments are closed.