በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች እየተካሄደ የሚገኘው የ2017 ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንደቀጠለ ነው
ከዚህም ጎን ለጎን በቀጣይ በተቋሙ ለሚካሄደው ሪፎርም ማስፈፀሚያ በተዘጋጀው መመሪያ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች እያካሄዱት የሚገኘው የ2017 ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንደቀጠለ ነው።
በዚህም መሠረት በዛሬው ዕለት ከቀትር በፊት የኦፕሬሽን ዘርፍ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ከቀትር በኋላም የዋና ዳይሬክተር ተጠሪ ልዮ ልዩ የሥራ ክፍሎች እና የተቋም ለውጥና ድጋፍ ሰጪ ዘርፍ የሥራ ክፍሎች የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀም በማቅረብ እንደሚያስገመግሙ ይጠበቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የተቋሙ የበላይ አመራሮች በተለያዩ የውይይት መድረኮች በመገኘት በባለሥልጣን መስሪያቤቱ የሚከናወነውን የሪፎርም አተገባበር በተመለከተ ግልፅነት መፍጠር የሚያስችል ገለፃ አድርገዋል።
በየውይይት መድረኮቹ ላይ የታደሙ የተቋሙ ሠራተኞች ላነሷቸው ጥያቄዎች ከመድረክ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
