+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ተግባርና ኃላፊነት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን መልሶ ማቋቋሚያ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 64/2011 መሠረት የተቋሙ ስልጣን ፣ ተግባርና ኃላፊነት ፤ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮችና ዋናዋና አገልግሎቶች

  1. የተቋሙ ስልጣንና ኃላፊነት

ባለስልጣኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  1. የመንገድ ኔትዎርክን፣ የመንገድ ስራን፣ የመንገዶችን አጠባበቅና አጠቃቀም ህግ ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
  2. የመንገድና ድልድይ ዲዛይን ደረጃ ያወጣል፤ ያሻሽላል፤ የጥገና ስታንዳርድ ያወጣል፤ የመንገድ ደረጃ አመዳደብ መመሪያ ያወጣል፤ አተገባበራቸውንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  3. የመንገድና ድልድይ ዲዛይን ከመጽደቁ በፊት በትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደርጋል፤
  4. የመንገድ እና የድልድይ ዲዛይን፣ ግንባታ፣ ጥገና ስራዎችን በራስ አቅም ያከናውናል፤ እንዲከናወን ያደርጋል፤
  5. ለመንገድ ሥራ የአዋጭነት ጥናት፣ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ፣ የመንገድ ዲዛይን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ጥናቶች ያካሂዳል፤ እንዲካሄድ ያደርጋል፤
  6. ለመንገድ ሥራው የሚያስፈልገውን ቦታ አግባብ ባለው ህግ መሰረት እንዲለቀቅ ያደርጋል፤
  7. አግባብ ባለው ህግ መሠረት የመንገድ ዲዛይን የሚሰሩ፣ የግንባታ ቁጥጥርና ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን የሚሰጡ አማካሪዎችን፣ በመንገድ ግንባታዎች ላይ የሚሰማሩ ሥራ ተቋራጮች የሚመረጡበትን ዘዴ ይወስናል፤
  8. ግንባታቸው የተጠናቀቀ መንገዶችና ሥራዎች በውሉ መሠረት በተፈለገው ጥራትና ደረጃ መከናወናቸውን በማረጋገጥ ይረከባል፤ እንዲረከብ ያደርጋል፤
  9. የመንገድ ፕላን መሰረት አዲስ ለሚገነቡ ለእግረኛ መተላለፊያ መንገድ የሚያስፈልገውን የመሬት ስፋትና አሰራር፤ የመንገድ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎችን ክብደት፣ ዓይነት ወሰን፤ ለተለያዩ የመንገድ ተጠቃሚዎች የሚውሉ መንገዶችን ለይቶ ይወሰናል፤ የመንገድ ምልክቶችን ይተክላል፤
  10. ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በመንገዶች ዳር እና መካከል የሚተከሉ የዛፍ ዓይነቶችና መጠን ይወሰናል፤ መተግበሩንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
  11. በዋና መንገዶች እና በመለስተኛ ዋና መንገዶች ግራ እና ቀኝ ዳርቻዎች፣ አካፋዮችና አደባባይ ላይ የአረንጓዴ ልማት ስፍራዎች ዲዛይን የመንገድ ግንባታ ፕላን አካል አድርጎ ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ መትከያ ስፍራዎችን ዝግጁ ያደርጋል፤ አስፈላጊውን መረጃ በወቅቱ ለተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ኤጀንሲ መረጃ ይሰጣል፤
  12. የአካባቢውን የውሃ ፍሰት መጠን ያገናዘበ የመንገዶችን ፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ይገነባል፤ ያስገነባል፤ ይጠግናል፤ ያሻሽላል፤
  13. መንገዶችን የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎቹን ጨምሮ ከደለል፣ ከሌላ ጉዳትና አለአግባብ ከመጠቀም ይጠብቃል፤ በመንገዶች ላይ የሚከሰቱ መሰናክሎችን ያስወግዳል፤ ወይም እንዲወገዱ ያደርጋል፤ በተገቢው መንገድ ያስተዳድራል፤
  14. በመንገድ ላይ ለሚከናወኑ የተለያዩየ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ቁፋሮዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ፈቃድ ይሰጣል፤
  15. ከሚለከታቸው የባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን በመንገዶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወይም ማናቸውንም መሰናክሎች የሚያስቀምጡ ወይም ነዳጅና ቅባት ነክ ፈሳሾችን የሚያፈሱ ሰዎችን አግባብ ባለው ህግ መሠረት እንዲጠየቁ ያደርጋል፤
  16. በህብረተሰቡ፣በቡድን፣ በግል ወይም በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት ለሚሰሩ መንገዶች ስታንዳርድ ያወጣል፤ ፈቃድይሠጣል፤ ይቆጣጠራል፤ እንዳስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤
  17. ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኮብልሰቶን መሰራት የሚገባቸውን መንገዶች ይለያል፤ በዕቅድ ውስጥ ያካትታል፤ የኮብልስቶን የሚጠርቡ ማህበራትን የአቅም ክፍተት በመለየት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
  18. የመንገድ ስራዎችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የላብራቶሪና ጥራት የማረጋገጥ ስራዎች አግባብ ያላቸውን የስራ ሂደቶች ተከትሎ ይፈፅማል፣ ያስፈፅማል፤
  19. መንገዶች አግባብ ባለው አካል እንዲሰየሙ ሃሳብ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ይተገብራል፤
  20. ለአረንጓዴ ልማት በከተማው ፕላን በተመለከተው መሰረት በቂ ስፍራ እንዲዘጋጅ እና እንዲከልል ያደርጋል፤
  21. የመንገድ አካፋዮችና ዳርቻዎች፣ የመከለያ አጥሮች ደረጃ እና ዲዛይን ያዘጋጃል፤
  22. ለጎርፍ የተጋለጡ የከተማ ክፍሎችን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ጥናት ያደርጋል፤ የመከላከያ ሥራ መስራት የሚያስችል ዲዛይን ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በህግ አግባብ ከስራ ተቋራጮች እና ከአማካሪዎች ጋር ውል በመዋዋል ግንባታው እንዲከናወን ያደርጋል፡፡