+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ አበባን ከቀድሞ ታሪኮቿ ጋር እያጣጣምን ዘመናዊ ከተማ እያደረግናት እንገኛለን።

ዛሬ 4 ኪሎ ፕላዛን፣ 4 ኪሎ የገበያ ማዕከልን እና መኪና ማቆሚያን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

የአገራችን ብሎም የከተማችን አበይት ታሪካዊ ስፍራ እና የድል ሀውልታችን መገኛ የሆነውን ፣ የተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶችን ያነበብንበትን፣ እውቀት የቀሰምንበትን፣ ስራ ፍለጋ ማስታወቂያ ለማንበብ የተመላለስንበትን የ4 ኪሎ አደባባይ አካባቢን መልሰን ገንብተን የያዘውን ግዙፍ ታሪክ የሚመጥን፣ ትላንታችንን ከዛሬ እና ከነገአችን ጋር የሚያገናኝ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ ዘመናዊ የከተማ ዲዛይን እና እሴት ያለው ውብ የ4 ኪሎ የገበያ ማዕከልን፣ መኪና ማቆሚያን እና 4 ኪሎ ፕላዛን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

ፕሮጀክቱ ከመሬት በታች የተገነቡ እጅግ ዘመናዊ 102 የስጦታ እና የአልባሳት መደብሮች፣ ካፌዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች ፣ ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ እና በአንድ ጊዜ እስከ 5 ሺህ ሰዎችን መሰብሰብ የሚያስችል የፕላዛ፣ የአንፊ ቴአትርና የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን ማቅረቢያ ስፍራዎችን የያዘ፤ የሲቪል ተሳትፎን፣ የባህል ዕድገትን፣ የእግር ጉዞን የሚያበረታታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው።

ፕሮጀክቱ ከወዲሁ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ የቱሪዝም ፍሰቱን በመጨመር ለዘርፉ ዕድገት የራሱ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚኖረው ይሆናል ።

ይህ ፕሮጀክት በታለመለት ልክ እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ክትትል ስታደርጉ የነበራችሁ ባለ ድርሻ አካላት፣ አመራሮች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.