በ2017 በጀት ዓመት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶች ተመርተዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2017 በጀት ዓመት ላከናወናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶችን በራስ ኃይል በማምረት ጥቅም ላይ አውሏል።
በጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓት ምርቶች የተመረቱ ሲሆን፤ በዚህም ቀደም ሲል በግዢ ይቀርብ የነበረውን የግንባታ ግብዓት በራስ አቅም መሸፈን ተችሏል፡፡
ባለፉት 12 ወራት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ማምረቻ ሳይቶች ተመርተው ጥቅም ላይ ከዋሉ የግንባታ ግብዓቶች መካከል፤ ልዩ ልዩ የካባ ምርቶች፣ ገረጋንቲ፣ ሰብ ቤዝ፣ ቤዝ ኮርስ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው የጠጠር ምርቶች፣ አስፋልት፤ ቱቦ እና ታይልስ ፣ እንዲሁም የማንሆል ክዳኖች ይገኙበታል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶችን የራስ አቅም ማመረት መቻሉ፤ በግብዓት እጥረት ምክንያት በመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች ላይ ይፈጠር የነበረውን መጓተት በማስቀረት፣ በተመጣጣኝ ወጪ በራስ ኃይል የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎችን በፍጥነት ለመፈፀም ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፡፡
