አዲስ አበባ፥ የስፖርት ቱሪዝም ዕውን ለማድረግ ፅኑ መሠረት ያስቀመጠች ከተማ!
የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ፣ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ያሳየችውን ልዕልና፣ በስፖርት ቱሪዝም ለመድገም ዝግጁነቷን ለዓለም እየገለጠች ነው። መንግስት ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ የሰጠው ትኩረት አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማስተናገድ ረገድ ያላትን አቅም ዕውን እየሆነ ነው።
ይኸውም፥ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ70 በላይ ስመ-ጥር ዓለም-አቀፍ አትሌቶች የሚሳተፉበት የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን የሩጫ ውድድርን (Addis Ababa Grand Prix One Day Meeting) ነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማስተናገድ መዘጋጀቷ በቂ ማሳያ ነው።
ውድድሩ የአትሌቲክስ እናት የሆነችውን ኢትዮጵያ፣ የዓለም አቀፍ ስፖርታዊ መዳረሻነት ደረጃዋን ከፍ የሚያደርግ፣ የስፖርት ቱሪዝም መልኅቁን የሚጥልባት እንድትኾን በር ከፉች ነው።
በዚሁ በያዝነው ሚያዝያ ወር ብቻ፣ ከቅዳሜው “የአንድ ቀን የሩጫ ውድድር” በተጨማሪ ሁለት ዓበይት ዓለማቀፍ ውድድሮች በከተማችን አዲስ አበባ ይከናወናሉ።
ነገ አዲስ አበባ ስታዲየም በዓለም አቀፍ አትሌቶች ብቃት እና በስፖርት አፍቃሪያን ድምቀት ትደምቃለች። ኢትዮጵያ በድጋሚ በአትሌቲክስ የዓለም ማዕከልነቷን ታረጋግጣለች።


Previous Post
Users Today : 4
Users Last 7 days : 199
Users Last 30 days : 847