የጎርፍ መከላከል ቅድመ-ዝግጅት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በዝናብ ወቅት የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል የግንባታ፣ ጥገና እና የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ፅዳት ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ መሆኑ ተገልፀጿል፡፡
ይህ የተገለፀው የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ፤ በስሩ ከሚገኙ የተለያዩ ስራ ክፍሎች ጋር የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ነው፡፡
የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መሐመድአወል ሰይድ እንደገለፁት፤ መጪው የክረምት ወቅት ከመግባቱ በፊት፣ ቀሪ የጎርፍ መከላከል ስራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በርብርብ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል፤ የጎርፍ ውሃ መውረጃ ቱቦዎችና ቦዮች በደለልና በቆሻሻ እንዳይዘጉ፤ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በየአካባቢው ማፅዳት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ፤ ጉዳት የደረሰባቸውን የጎርፍ ማስወገጃ መስመሮች ፅዳትና መጠገን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ክፍት የሆኑ ማንሆል ክዳኖችን መልሶ በመክደን ለትራፊክ ፍሰቱ ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት አብይ ተግባር መሆኑን ኢንጅነር መሀመድአወል አስታውቀዋል።


Previous Post
Next Post
Users Today : 12
Users Last 7 days : 191
Users Last 30 days : 845