+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ አበባ በአምስት አመት ከ 60 ሺ በላይ ፕሮጀክቶችን ገንብታለች !

አዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ወዲህ በተለይም በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ በርካታ ፕሮጀክቶችን በብቃት ሰርታ አጠናቃለች፡፡ በዋናነትም በመሰረተ ልማት እና በመንገድ ግንባታ ከተማዋን የማይመጥን እና አነስተኛ የነበረውን የከተማዋ የመንገድ ስፋት ሌት ተቀን በመስራት ከለውጡ ወዲህ እና ባለፉት አምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ከ1ሺ 500 ኪ.ሜ በላይ የመንገድ ግንባታዎችን መገንባት ችላለች፡፡ በተጨማሪም የከተማዋ የውሃ አቅርቦትና አቅም ከነበረበት ላይ 40 በመቶ በመጨመር ሰፊ ስራ መስራት ተችሏል፡፡

ከሁሉም በላይ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቅረፍ የሚያስችሉና ገቢያውን ለማረጋጋት የሚረዱ የገቢያ ማዕከላትን በማስፋትና በማዘመን አምራችና ሸማቹን በቀጥታ ማስተናገድ የሚያስችሉ 6 የገቢያ ማዕከላትን መገንባት ችለናል፡፡ በተጨማሪም ግዙፍ የግብርና የልህቀት ማዕከል በመገንባት በቀን 60 ሺ እንቁላል ማምረት የማትችል የነበረችው አዲስ አበባ ፤ አሁን ላይ በቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ማቅረብ ችላለች፡፡ በነዚህ የልማት ስራዎች ከተሞች የህንፃ ጫካ ብቻ ሳይሆኑ ማምረት የሚችሉ ሁሉን አቀፍ መሆናቸውን አሳይተናል፡፡

በአጠቃለይ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ የውሃ ፣ የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እንዲሁም ማህበረሱቡ በከፍተኛ ሁኔታ ጥያቄ ያነሳባቸው የነበሩ እንደ ጤናና የትምህርት ተቋማት ፣ የህፃናት መጫወቻ ሜዳ እና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያዎች ጨምሮ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ከ60 ሺ በላይ ፕሮጀክቶችን ገንብተን ለህዝባችን አስረክበናል፡፡ ከዚህ ቁጥር ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ማህበረቡ የልማት ጥሪውን ተቀብሎ በጉልበቱ በገንዘቡ እና በእውቀቱ ተሳትፎ ያደረገባቸው ናቸው ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.