+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ መንደር የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ ግንባታ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ መንደር የአስፓልት መንገድ ግንባታ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኘው ይህ የውስጥ ለውስጥ መንገድ በአጠቃላይ 1.3 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ነው፡፡

አሁን ላይ ሰቤዝ የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ የመንገድ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ፤ የኢንዱስትሪ መንደሩ የሥራ እንቅስቃሴ እንዲቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡

የፕሮጀክቱን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን የባለሥልጣን መስሪያቤቱ የደቡብ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

Comments are closed.