+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል የሚያስችሉ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው

መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ለድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በጥናት በመለየት፣ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል የቅድመ-መካከል ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ፤ የክረምት ወቅት የጎርፍ አደጋ ስጋት ሊከሰትባቸው የሚችሉ 20 የተለያዩ ቦታዎችን በጥናት በመለየት፣ የድሬኔጅ ግንባታና የጥገና ስራዎችን በማከናወን ዘላቂ መፍትሔ እየሰጠ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ ከተለዩት 20 ቦታዎች መካከል፤ 11 የሚሆኑት ላይ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

የጎርፍ አደጋ ቅድመ-መከላከል ሥራ እየተከናወነ ከሚገኝባቸው ሥፍራዎች መካከል፤ ጀርመን ድልድይ፣ ሃና ማርያም ወረዳ 9፣ ቃሊቲ ጉምሩክ-ትራፊክ፣ ከቃሊቲ – ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት፣ ቡልቡላ ድልድይ፣ ጉርድ ሾላ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳ እና ቤተል ድልድይ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

Comments are closed.