የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ፦
የመንገድ መሠረተ ልማት፡- 135 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ፣ 246 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣141 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣ 43 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣ 53 የተሽከርካሪ እና እግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች፤190 ኪ.ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ሥርዓት ዝርጋታና፣ 83 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ሥራ ተሰርቷል።
የትራንስፖርት ሥርዓት ለማሳደግ ፦ 153 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣ በአንድ ጊዜ 35,000 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸውና 33 የባስ እና ታክሲ ዘመናዊ ተርሚናሎች፣
የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ፦ 1,122 ስማርት እና 1708 ኖርማል በአጠቃላይ 2830 የመብራት ምሰሶዎች ተተክሏል፤ 179.6 ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፤ 5,048 የኤሌክትሪክ ምሰሶ ማዛወር፤ 22.41 የመሬት ውስጥ መካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር መቅበር፤ 324 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችና 7.9 ኪ.ሜትር ፒቪሲ ዝርጋታ ሥራ ተሰርቷል።
የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎችን ማስፋፋት፦ የአረንጓዴ ልማት ፤ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች ፤ ዘመናዊ የመንገድ ዳር የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets)፣ ስፍራዎች ተገንብተዋል።
