የፉሪ ሃና የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል
የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ ፉሪ ሀና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 5 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ከ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነው የመንገዱ ክፍል በአስፋልት፣ ቀሪው 1 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የፕሮጀክቱ ክፍል ደግሞ በኮብል ንጣፍ የሚሸፈን ነው፡፡
የመንገድ የግንባታው ኩሽላደር ኮንስትራክሽን በተባለ የሥራ ተቋራጭ እተየገነባ የሚገኝ ሲሆን፤ የማማከርና የቁጥጥር ሥራው ደግሞ አይዲኮን የተባለ አማካሪ ድርጅት እያከናወነው ይገኛል፡፡
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የተቋሙ የሥራ መሪዎች ቡድን የግንባታ ሥራው የሚገኝበትን ደረጃ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
አሁን ላይ የአሰፋልት ግንባታ በሚካሄድበት የፕሮጀክቱ ክፍል፤ የአፈር ቆረጣ እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ የፉሪ ሀና የጋራ መኖሪያ ቤት የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
ኢንጂነር ሙህዲን አክለውም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ እንዲፋጠን አስፈላጊውን ድጋፍና የቅርብ ክትትል እንደሚያደርግ ጠቁመው፤ የሥራ ተቋራጩ የግንባታ ስራውን ከተያዘለት 570 ቀናት ጊዜ በፊት ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡


Previous Post
Users Today : 53
Users Last 7 days : 323
Users Last 30 days : 1178