+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ወጂ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የድልድይ ግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት13 ቀን 2017 ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ወጂ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የድልድይ ግንባታ በማከናወን ላይ ነው፡፡

በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የወጂ ድልድይ ፕሮጀክት 14 ሜትር ርዝመት እና 30 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

የድልድዩ ግንባታ ከወንዙ ጠለል በላይ 10 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን አሁን ላይ የቁፋሮ እና የግንብ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ፊዚካል አፈፃፀም 23 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

የድልድዩ ግንባታ ለአከባቢው ነዋሪዎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መፋጠን ከሚኖረው ፋይዳ ባሻገር፤ ከጎሮ አደባባይ ወደ ሰሚት ጊዮርጊስ አቅጣጫ እና አካባቢው መጓዝ ለሚፈልጉ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ በመሆን የአካባቢውን የትራፊክ ፍሰት ለማቃለል እገዛ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ የሚገኙና ለረጅም ዓመት አገልግሎት በመስጠት ጉዳት የደረሰባቸውን ድልድዮች ከመጠገን በተጨማሪ በተለያዩ አካባቢዎች ኣዳዲስ ድልድዮችን በመገንባት ለህብረተሰቡ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመሰጠት እየሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.