+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ሳምንታዊ ወርቃማው ሰኞ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ወርቃማዉ ሰኞ የልምድና ዕዉቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬው መርሃ ግብሩ ላይ የባለሥልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ራሄል ደረሰ በህይወት ክህሎትና ሥነ- ምግባር ፅነሰ ሀሳብ ላይ ትኩረት አድርገው ለባለሥልጣኑ አመራሮችና ሠራተኞች ገለፃ አድርገዋል፡፡

ወ/ሮ ራሄል እንደገለፁት፤ የህይወት ክህሎት የባህሪ፣የአመለካከትና የእሴት ድምር ውጤት መሆኑን ጠቁመው፤ በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ ለመሆን የህይወት ክህሎታችንን በተለያዩ መንገዶች ማዳበርና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበስን መሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በተመሣሣይም ባለፈው ሣምንት በወርቃማው ሰኞ መርሃ-ግብር ላይ የጊዜ አጠቃቀም ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት ባለው ፋይዳ ላይ ያተኮረ ገለፃ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተቋም ለውጥና ሲስተም ዲዛይን ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑት በአቶ ሙሉጌታ ፍቅሬ መቅረቡ ይታወሳል።

Comments are closed.