በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ በአጠቃላይ ይዘቱም፦ ፦
ባለ14 ወለል ህንፃ፣ 2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶችን፣
የቲያትር አዳራሽ ፣ 3 የተለያዩ አዳራሾችን ፣
የሆቴል እና ሪስቶራት ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችን እና ፓርኪንግ አገልግሎት ይዟል ።
የጥበብ ስራ በአዳራሽ ብቻ የተወሰነ ባለመሆኑ እና ወደ ማህበረሰቡ ቀረብ እንዲል፤ በከተማችን በተገበርነዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ የተለያዩ የዉጭ የኪነ ጥበብ ስራ የሚከወንባቸዉ ከ 160 በላይ አንፊ ቲአትርና ፕላዛዎች ተገንብተው ለአገልግሎት አዉለናል ።
