ሣምንታዊ የመንገድ ጥገና መረጃ
መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ ፡- በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ጉዳት የደረሰባቸውን መንገዶች በመጠገን ለትራፊክ እንቅስታሴ ምቹ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በሣምንቱ ጥገና ስራ ከተደረገላቸው መንገዶች መካከል ከለገሀር – ቂርቆስ፣ ከሰሚት 72 – አራብሳ፣ ከጎሮ – ፊጋ፣ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ – አደይ አበባ የሚገኙት መንገዶች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በቀጣይም በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙና ጉዳት የደረሰባቸውን መንገዶች በመለየት ተከታታይነት ባለው የመንገድ ጥገና ስራ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
