+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም:- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አመራርና ሰራተኞች የዘንድሮውን 130ኛውን የአደዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ‘’የአድዋ አደራ፣ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ማንሰራራት’’ በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት አካሂደዋል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ ሱለይማ ዓሊ እንደተናገሩት፤ አድዋ የኢትዮጵያውያን ኩራት፣ የአንድነት፣ የፅናትና የማንነት መገለጫ እንዲሁም ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከአድዋ ድል በዓል አንድነት፣ ፅናትንና ክብርን እንማራለን ያሉት አቶ ሱለይማን፤ የአደዋ ድል መንፈስን በመላበስ ሀገራችን የአፍሪካ ብሎም የዓለም ተምሳሌት እንድትሆን አንድነትን በማጠናከር በተሰመራንበት የስራ መስክ ውጤታማ መሆን ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ሰሎሞን በበኩላቸው፤ የመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል አብነት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ጠበቃ፣ በራስ አቅም ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ በምታካሂደው ብዝሃ-ምጣኔ ሀብት እድገት፣ ዜጎች በንቃትና በትጋት ሊሳተፉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አቶ ኢያሱ አክለውም፤ በአድዋ ድል ታሪክ ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ፣ጠንካራ ሀገራዊ አንድነት መፍጠር፣ ሀገራዊ ጥቅምን ማስከበር፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ማፅናትና የተጀመረውን ሀገራዊ ብልጽግና ማስቀጠል ከዛሬው ትውልድ የሚጠበቅ መሆኑን አስረድተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ አደዋ የትናንት ድል፣ ለዛሬ ኩራት፣ ለነገ ደግሞ ስንቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን የአድዋ ታሪክን ልንደግመው ይገባል ብለዋል፡፡

Comments are closed.