ከለቡ መድኃኒዓለም ወደ ጀሞ 3 የሚያገናኝ አቋራጭ መንገድ እየተገነባ ነው
መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ከለቡ መድኃኒዓለም ወደ ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ የሚወስድ አጭር እና አቋራጭ መንገድ እየተገነባ ይገኛል።።
ቀደም ሲል የኮብል ንጣፍ የነበረውን ነባር መንገድ ደረጃ በማሻሻል በአስፋልት ለመቀየር እየተሠራ ሲሆን፤ የግንባታ ስራው በአጠቃላይ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 7 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው።
አሁን ላይ 1 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመር ቱቦ ቀበራ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ የከርቭ ስቶን ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል።
የመንገዱን ቀሪ የግንባታ ሥራዎች በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
የመንገዱ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፤ ከለቡ መድኃኒዓለም ወደ ጀሞ 3 እና ተቃራኒ አቅጣጫ፤ እንዲሁም ፉሪ አካባቢን በማገናኘት በአካባቢው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላየ የሚኖረውን የትራፊክ ጫና ለመቀነስ ከፍተኛ ጠቀሜታ የኖረዋል።


Previous Post
Next Post
Users Today : 13
Users Last 7 days : 337
Users Last 30 days : 1253