+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም-አስኮ ጨረታ መገንጠል (ኒኮላ) መንገድ ማስፋፊያ ስራ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአስኮ ታክሲ ተርሚናል- ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም የሚወስደው መንገድ የትራፊክ ፍሰት ለማሻሻል የጀመረው የማስፋፊያ ስራ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሰራል ይገኛል፡፡

የፕሮጀክቱ መሀንዲስ የሆኑት ሄኖክ ምትኩ እንደገለፁት፤ የማስፋፊያ ስራው በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል ምዕራብ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ አጠቃላይ የመንገዱ ርዝመት 830 ሜትር ይሸፍናል ብለዋል፡፡

የግንባታው ሂደት አሁን ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ መሀንዲሱ ገልፀዋል።

መሀንዲሱ አክለውም፣ በቀጣይ የእግረኛ መንገድ እና ተያያዥ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ መንገዱን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ ባለሥልጣኑ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀደምሲል የነበረው መንገዱ ስፋት 7 ሜትር ሲሆን፤ አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው የማስፋፊያ ስራ የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ወደ 15 ሜትር የጎን ስፋት ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የመንገድ ማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Comments are closed.