በከተማዋ በሚገነባው የፈጣን አውቶቢስ መስመር ግንባታ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ
በአዲስ አበባ ከጀሞ3 እስከ ፒያሳ የሚገነባው የፈጣን አውቶቢስ መስመር ግንባታ በተመለከተ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለወረዳ 5 ነዋሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የግንባታ ፕሮጀክቶች ኮንትራት ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት ኢንጅነር ሙሉቀን ዋቅጋሪ እንደገለፁት፤ የፈጣን አውቶብስ መስመር ግንባታ ዋናው ዓላማ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት የሚፈጠሩ መዘግየቶችን ለመቀነስ አውቶቢሶች ብቻ የሚጠቀሙበት ልዩ መስመር በመገንባት ለተጓጓዦች ተጨባጭ ጠቀሜታ የሚሰጥና ለከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋፆኦ የሚያበረክት ነው ብለዋል።
የፕሮጀክቱ ትግበራና ክትትል ባለሙያ አሸናፊ ንጉሴ በበኩላቸው፤ ይህ የፈጣን አውቶቢስ መተላለፊያ መስመር ግንባታ በታሰበው ጊዜ ለማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው፤በግንባታው ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን ካሉ ህብረተሰቡ ለባሥልጣን መስሪያቤቱና በአቅራቢያ ለሚገኙ ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ አስተዳደር በማሳዉቅ መፍትሄ እንደሚሰጠው ገልፀዋል።
ከዳግማዊ ሚኒሊክ አደባባይ-በአንዋር መስጊድ- ተክለኃይማኖት- ሜክስኮ – ቄራ – ጎፋ ገብርኤል- ጀርመን አደባባይ – ጀሞ ሚካኤል – ጀሞ3 የሚዘልቀው የፈጣን አውቶቢስ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት 15 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ሲሆን፤ ከፈረንሳይ መንግስት የልማት ኤጄንሲ በተገኘ ብድር እና በከተማ አስተዳደሩ በጀት የሚገነባ ፕሮጀክት ነው፡፡
የውይይት ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፣ ለልማቱ ያላቸውን ድጋፍ የገለጹ ሲሆን፣ ግንባታው ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት ጊዜ እስቀሚጠናቀቅ በጉጉት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።


Previous Post
Next Post
Users Today : 23
Users Last 7 days : 288
Users Last 30 days : 1253