+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራት ተካሄደ

ታህሣስ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ አየር ጤና አካባቢ በሚገኘው ተስፋ የምገባ ማዕከል ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ማዕድ አጋርቷል።

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ዶሌቦ፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከመደበኛ ተልዕኮው ባሻገር፣ በተለያዩ መስኮች ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚኘኝ ገልፀዋል።

በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህበረተሰብ ክፍሎችን ከመደገፍ አንፃር ባለፉት ዓመታት በማዕድ ማጋራት፣ በአልባሳት ማሰባሰብ እና በተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎች ተቋማዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን አውስተዋል።

በያዝነው ዓመትም በአቅመ-ደካሞች ቤት እድሳት፣ በተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጥገና፣ በህፃናት ድጋፍና እንክብካቤ እንዲሁም በሌሎች መስኮች ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሁሉም ማህበራዊ ችግሮች በመንግሥት አቅም ብቻ የሚፈቱ ባለመሆኑ፤ ሌሎች አካላትም የበኩላቸውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚ ሙሄ በበኩላቸው፤ የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች በጋራ ተሣትፎ ለመፍታት እየተደረገ ባለው ጥረት ተቋማትና ግለሰቦች እያበረከቱት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ጠቅሰው፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ ከመደበኛ ተልዕኮ ባሻገር በማዕድ ማጋራት ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Comments are closed.