+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

እንኳን ለጌታ እየሱስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዛሬ የመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓልን ለማህበራዊ ችግር ከተጋለጡ ወገኖች ፣ የአገር ባለውለታ አረጋውያን፣ አቅመ ደካሞችና ደጋፊ ከሌላቸው ወገኖቻችን ጋር በጉለሌ ‘ተስፋ ብርሃን’ የምገባ ማዕከል ማዕድ በመቋደስ አክብረናል።

እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ከመቀበል ይልቅ በመስጠትና በማካፈል ውስጥ ነው። የከተማችን በረከቶች ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር በዓልን ማክበር ለእኛ ታላቅ ክብርና የሞራል ስንቅ ነው። በዛሬው ዕለትም በሁሉም 26ቱ የከተማችን የምገባ ማዕከላት የማዕድ መቋደስ መርሃ ግብር በድምቀት ተካሂዷል።

በድጋሚ መልካም በዓል !

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.