የጎርፍ ተጋላጭነትን መከላከል የሚያስችል የጥገና ስራ እየተካሄደ ነው
ታህሣስ 26 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን፤ በክረምት ወራት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የማስተካከያ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የጎርፍ መከለከልና ድንገተኛ ስራዎች ቡድን መሪ ኢንጅነር ቀልቤሳ ቢቲማ፤ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ እና የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ድልድዮችንና የድሬኔጅ መስመሮች እየተጠገኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግንባታ እና የጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሉካንዳ ድልድይ ተብሎ የሚጠራው፣ ዮሐንስ ፀበል አካባቢ የሚገኝው ድልድይ እና አስኮ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች 390 ሜትር ርዝመት ያለው የድሬኔጅ መስመር ግንባታ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል፡፡
በዮሐንስ ፀበል አካባቢ ነዋሪ የሆነው ወጣት ኡመር ሀሰን፤ ቀደም ሲል አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ድልድይ ለተሽከርካሪና ለእግረኞች እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እንደነበር አስታውሶ፤ አሁን ላይ ድልድዩ ምቹ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር በሚያስችል ሁኔታ እየተገነባ መሆኑ ችግሩን እንደሚፈታ ተናግሯል፡፡
መንገዱ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል እና አበበች ጎበና የህፃናት ማሳደጊያ አቅጣጫ የሚያቋርጥ እና በርካታ ነዋሪዎች የሚጠቀሙበት መንገድ በመሆኑ፤ የድልድይ ግንባታው በዚህ ደረጃ መከናወኑ ለአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ወጣት ኡመር ጨምሮ ገልጿል፡፡


Previous Post
Next Post
Users Today : 39
Users Last 7 days : 286
Users Last 30 days : 1205