በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የመክፈት ሥራ እንደቀጠለ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በግብረ-ኃይል የማስከፈት ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል።
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ፤ የማዕከላዊ መንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር፤ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በሚገኙ የተለያዩ አካባቢው በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ክፍት አድርጓል።
በተመሳሳይም፤ የምዕራብ መንገድ ኔትዎርክ ማኔጅመንት ከወረዳ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት፤ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 7፣ ልዩ ቦታው ጥቁር አባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ በአጥር የተዘጉ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አሰከፍቷል።
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከታህሳስ 15 ጀምሮ እያከናወነ ባለው የመንገድ መብት ማስጠበቅ ሥራ በበርካታ ሥፍራዎች መንገድ የተዘጋባቸውን አጥሮች ማንሳት ችሏል።
በሌሎች አጥር ባልተነሳባቸው ሁሉም የከተማዋ ክፍሎች እየወደሰ ያለው ርምጃ በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡


Previous Post
Next Post
Users Today : 26
Users Last 7 days : 282
Users Last 30 days : 1032