ዛሬ የሃባሪ ሜዲካል ፕላዛን መርቀን በይፋ ሥራ አስጀምረናል።
ተቋሙ ለሀገራችን ጥራት ያለው የሕክምና አማራጭ ይዞ የመጣ ማዕከል ነው። ሃባሪ ሜዲካል ፕላዛ ዜጎች ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ጉዞ በማስቀረት፣ ጥራት ያለው አገልግሎት በሀገር ውስጥ ለማቅረብ የጀመረው ጉዞ ተስፋ ሰጪ ነው።
ተቋሙ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ ሁሉን አቀፍ ድጋፋችን አይለያችሁም።
ለዚህ በጎ ጅምር እና ለላቀ አገልግሎታችሁ ያለኝን አድናቆት እየገለጽኩ፤ ለተቋሙ ስኬታማ የሥራ ዘመን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Previous Post
Next Post
Users Today : 26
Users Last 7 days : 282
Users Last 30 days : 1032