በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሱ ህገወጥ ተግባራትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሱ ህገ-ወጥ ተግባራትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በኮተቤ ካራ አካባቢ በእግረኛ መንገድ ላይ መደበኛ ያልሆነ የንግድ ስራ ሲያከናውኑ የነበሩ ግለሰቦችን ከየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር፣ ከፖሊስና ከደንብ ማስከበር አባላት ጋር በመቀናጀት የመከላከልና የቁጥጥር ስራ አከናውኗል፡፡
በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሰሜን አዲስ አበባ የመንገድ ሀብት ቁጥጥር ቡድን መሪ ወ/ሮ ዓለም ጌታቸው፤ መንገድ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተከናወነ የሚገኘው ሥራ የተሻለ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳትየሚደርሱ ህገ*ወጥ ተግባራትን ለመካከልና ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ ዓለም ጨምረው ገልፀዋል፡፡


Previous Post
Next Post
Users Today : 30
Users Last 7 days : 261
Users Last 30 days : 1169