+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

“በመደመር መንግስት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ

ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም፤ አበባ አበባ፤ በመደመር መንግሥት ዕይታ፤ የከተማ ልማት፣ የቱሪዝም፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ላይ ትኩረት አድርጎ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቋል።

በግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ላይ ትኩረት በማድረግ የሥልጠና ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሬገላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ፀጋዬ ቦርሴ፤ በዘርፎቹ የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ ያጋጠሙ ፈተናዎች እና ለዘላቂ ብልፅግና ሠራተኛው ሊኖረው በሚገባው ሚና ላይ ገለፃ አድርገዋል።

በሥልጠናው ላይ የዘርፎቹ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ ሀገሪቱ ባለፉት ዘመናት ያለፈችባቸው ሂደቶችና ከለውጡ በኋላ የተመዘገቡ ስኬቶች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተዳስሰዋል።

በሁለቱ የሥልጠና ቀናት በቅርቡት ሰነዶች ላይ ተሣታፊዎች ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ ሠራተኞች በተሰለፉበት የሥራ መስክ የሀገሪቱን ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚኖራቸው ሚና ዙሪያየጋራ መግባት ላይ ተደርሷል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ፤ በሥልጠናው ላይ የተነሱትን ገንቢ ሀሳቦች ወደ ተቋማችን በማምጣት፣ እንደ ከተማ ብሎም እንደ ሀገር የተቀመጡትን ትልሞች ከማሳካት አንፃር የመንገድ ዘርፉ ተዋንያን ሚና የጎላ መሆኑን በመገንዘብ፣ የላቀ ውጤት ለማስገንዘብ መረባረብና ለሀገራችን ብልጽግና የራሳችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመጨረሻም የሥልጠናው ተሣታፊዎች ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት፤ የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የዜግነት ድርሻቸውን በላቀ ደረጃ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

Comments are closed.