+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የውስጥ ለውስጥና የአክሰስ መንገዶችን ችግር ለማቃለል የመቃረቢያ መንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራ እየተከናወኑ ነው

መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ፡- ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የአዲስ አበባ የመንገድ መሰረተ ልማትን በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የአክሰስ መንገድ ግንባታና ጥገና ስራ በስፋት እያከናወነ ነው፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ እና የመንገድ ሽፋኑን ለማሳደግ የአክሰስ መንገዶች ግንባታና ጥገና ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ በያዝነው በጀት ዓመት በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት የመቃረቢያ መንገዶች ግንባታና ጥገና ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን የመቃረቢያ መንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራው በተለይም በአዳዲስ የመኖሪያ መንደሮች፣ የልማት ተነሺዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች እና በአርሶ አደር መንደሮች አቅራቢያዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡የመቃረቢያ መንገድ ግንባታና ጥገና ሥራው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ኃይል እና በስራ ተቋራጮች እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን አጠቃላይ ከ103 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት እና በአማካይ ከ7-15 ሜትር የጐን ስፋት የተሰሩ ናቸው፡፡ ከ341 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመከናወን ላይ የሚገኙት የመቃረቢያ መንገዶች የህብረተሰቡን የመግቢያና መውጪያ መንገድ ችግር በመፍታት የየአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖራቸው ይታመናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *