+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በዓይነቱ ልዩ የሆነው የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 90 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፡- መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የግንባታ ስራው መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም የተጀመረው የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታ አሁን ላይ 90 በመቶ ተጠናቋል፡፡በከተማችን የመንገድ ግንባታ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የዋሻ ውስጥ መተላለፊያ መስመር ጨምሮ ተሻገጋጋሪ ድልድይ እና የፈጣን አውቶብስ መመላለሻ ኮሪዶርን አካቶ እየተገነባ የሚገኘው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 3.8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30-45 ሜትር የሚሆን የጎን ስፋት አለው። ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ጎተራ ማሳለጫ የሚወስደው ዋና መንገድ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ አሁን ላይ ከቄራ እና ከቂርቆስ ወደ ጎፋ ማዞሪያ በሚወስዱት መንገዶች መጋጠሚያ ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የማሳለጫ ድልድዩ መቃረቢያ መንገዶች የሙሌት እና የሰብ ቤዝ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።