+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለፉት 8 ወራት 95 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኮብል ስቶን መንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራ ተከናውኗል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት 8 ወራት 95 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የኮብል ስቶን መንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች አከናውኗል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የተሳለጠ ለማድረግ እና የመንገድ ሽፋኑን ለማሳደግ በ2014 በጀት ዓመት 91 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ አዳዲስ የኮብል መንገዶችን ለመገንባት አቅዶ ባለፉት 8 ወራት ብቻ ከ62 ኪሎ ሜትር በላይ የኮብል መንገድ መገንባት ችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ 50 ኪሎ ሜትር የኮብል ስቶን መንገድ ለመጠገን አቅዶ ከ32 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የኮብልስቶን መንገዶች ጥገና አካሂዷል፡፡የኮብል መንገድ የጥገና ስራው በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተከናወነ ሲሆን በፍሳሽ መስመሮች ዝርጋታ ምክንያት የተቆፋፈሩ መንገዶች በጥገና ሥራው ተካተው መልሰው እንዲገነቡ ተደርጓል፡፡ ከጥገና ስራው ጎን ለጎንም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ለማዘመን እና የጋራ መኖርያ ቤት አካባቢ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎችን በመንገድ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

Comments are closed.