+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ መንገድ ፕሮጀከት ግንባታ 77 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የራስ ሃይል እየተገነባ የሚገኘው የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 77 በመቶ ተከናውኗል፡፡ የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀከት አጠቃላይ 5.7 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 25 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡አሁን ላይ ከመንገዱ አጠቃላይ ርዝመት ውስጥ 4.8 ኪሎ ሜትር በሚደርሰው የመንገዱ ክፍል ላይ አስፋልት የማልበስ ስራ ተከናውኗል፡፡ በቀሪው የመንገዱ ክፍል ደግሞ የአስፋልት ስራ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመካሄድ ላይ ሲሆን ከዚህም ጎን ለጎን የእግረኛ መንገድ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ይሁን እንጂ በመንገድ ፕሮጀክቱ የወሰን ክልል ውስጥ እስካሁን ድረስ ያልተጠናቀቁ የወሰን ማስከበር ስራዎች በመኖራቸው ግንባታው በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡አሁን ላይ በመንገድ ፕሮጀክቱ የእግረኛ መንገድ ላይ ከሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎች መካከል በርካታ የመብራት ምሰስዎች እና የቴሌ መስመሮች ይገኙበታል፡፡ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ከማሳደጉም በተጨማሪ ከቃሊቲ ቶታል ወደ አቃቂ ከተማ እና ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ለመሄድ በአቋራጭነት የሚያገለግል መንገድ ይሆናል፡፡

Comments are closed.