+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የጥገና ስራዎች እየተከናወኑ ነው

መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የሕብረተሰብን የዕለት ተለት የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገዶችን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃን ለማሳደግ የሚያስችሉ በቀለበት፣ ዋና እንዲሁም አቋራጭ መንገዶች ላይ ሁሉን አቀፍ የጥገና ስራዎችን በማከናወን የሕብረተሰቡን የዕለት ተለት ማህበራዊና አኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጎልበት ያልተቆጠበ ጥረቱን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ከተከናወኑ የአስፋልት መንገድ ጥገና ስራዎች ውስጥ ከጐፋ መብራት – ብሔረጽጌ፣ ከሆላንድ ኤምባሲ – 18 ማዘሪያ ፈጣን የቀለበት መንገድ ክፍል፣ ሽሮሜዳ ወረዳ 23 ስላሴ ቤ/ክ አካባቢ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ባለሰልጣኑ በቀጣይ በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መንገዶችን በመለየት የመንገድ ጥገና ስራዎችን በተጠናቀረ መልኩ የሚቀጥል ሲሆን መንገዶችን ለብልሽት የሚዳርጉ ህገወጥ ድርጊቶችን በመከላከልና በመጠበቅ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ መንገዶችን በመፍጠር ህብረተሰቡ በጋራ ሀብቱ ላይ እንዲሰራ ባለስልጣኑ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

Comments are closed.