“በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ የሚሰጠው ስልጠና እንደቀጠለ ነው
ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ “በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ቀጥሏል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል ዴሌቦ፤ የስልጠናው ዓላማ የመደመር መንግስት ዋና ዋና የትኩረት ዘርፎችን በማስገንዘብ፣ ሠራተኛው በተሰለፈበት የሥራ መስክ የበኩሉን አውንታዊ ሚና እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው በ አራት ዘርፎች ማለትም በከተማ ልማት፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና ልማትና በቱሪዝም ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑን አቶ ጀማል ጠቅሰዋል።
የለውጡ መንግስት የእስካአሁን ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና ቀጣይ ትልሞች በዝርዝር መቅረባቸውን የገለፁት አቶ ጀማል፤ የስልጠናው ተሣታፊዎች በቡድን ውይይቶች የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነትን የሚያጠናክር ግልፅነት መፈጠር መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
የስልጠናው ተካፋዮች በሰጡት አስተያየት፤ ስልጠናው ከለውጡ ወዲህ የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመገንዘብ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ግልፅነት መፍጠሩን ተናግረዋል።
በተለይም ከከተማ ልማት ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ እንደመሆኑ፣ የተሰሩትን ስራዎች ለትውልድ ከማቆየትና በቀጣይ የቅንጅት እና በጋራ የመስራት ስርዓትን የሚያጠናክር ይሆናል ብለዋል።


Previous Post
Next Post
Users Today : 30
Users Last 7 days : 261
Users Last 30 days : 1169