+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የኮሪደር ልማቱ ትሩፋቶች የሆኑት የንግድ ቤቶች እና ፕላዛዎች

ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች መነሃርያ እንደመሆንዋ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ውብ ፅዱና ማራኪ እንዲሁም የቱሪዝም መናገሻና ተወዳዳሪ ለማድረግ ደረጃዋን የጠበቀች ውብ ከተማ በመገንባት ሂደት በኮሪደር ልማት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል :: የኮሪደር ልማቱም ካስገኛቸው ትሩፋቶች መካከል የንግድ ቤቶች እና ፕላዛዎች በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በዚህ በኮሪደር ልማቱ ብቻ 5200 የንግድ ሱቆች እና ፕላዛዎች ተገንብተዋል ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 4972 ለተጠቃሚዎች ተላልፈው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ::

የተሟላ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ከከተሜነት እድገት ጋር የተሳሰረው የኮሪደር ልማት ያስገኛቸው እነዚህ ንግድ ቤቶች እና ፕላዛዎች ከዚህ ቀደም ለመገልገልም ሆነ ለእይታ ምቹ ያልነበሩ ንግድ ቤቶች ተነስተው በምትካቸው የአካባቢውን ውበት በቀየሩ እና እይታን በሚስቡ ዘመናዊ ሱቆች እና ፕላዛዎች በመተካታቸው ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ከመሆን ባለፈ በዋናነት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው::

እነዚህ የንግድ ሱቆቹ የከተማዋን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ፤ የኑሮ ውድነትን በመቅነስ እና ገበያውን በማረጋጋት ረገድም የጎላ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ቀሪዎቹ 228 ሱቆችም በቀጣይ ጥቂት ቀናት ወደ ስራ የሚገቡ ይሆናል፡፡

ለከተማችን እድገትና ለህዝባችን ተጠቃሚነት እንተጋለን!!!

Comments are closed.