የአየር ጤና – ወለቴ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን ለማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የስትራቴጂክ አመራር አባላት የአየር ጤና- ወለቴ የመንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ለማፋጠን የሚያስችሉና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡
የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ የመንድ ፕሮጀክቱ በወሰን ማስከበርና ተያያዥ ችግሮች የተነሳ ለረጅም ጊዜ የግንባታ ሂደቱ መጓተቱን አውስተው፤ በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ የግንባታ ሂደቱ የሚፋጠንበትን ሁኔታ ለማገዝና ድጋፍ ለማድረግ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኢንጂነር ሙህዲን አክለውም በአሁኑ ወቅት በመንገድ ፕሮጀክቱ የግንባታ ስራ ላይ ማነቆ ሆነው የቆዩ የወሰን ማስከበር ስራዎች መጠናቀቅ በመቻላቸው የስራ ተቋራጩ በሙሉ አቅሙ የግንባታ ስራውን እንዲያከናውን አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን፤ችግሩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ግን የኮንትራት ውል እስከማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል ።


Previous Post
Next Post
Users Today : 25
Users Last 7 days : 332
Users Last 30 days : 987