+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ሰላምና ፀጥታን በተመለከተ

በሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት በአካባቢ ሠላም፣ በአብሮነትና ትብብር የሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ በድግግሞሽ ከ7.9 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በግንዛቤ በብሎክ የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክር መድረኮች ላይ ማሳተፍ ተችሏል፡

👉በማኅበረሰብ አቀፍ ፀጥታ አጠባበቅ ላይም አካባቢን በመጠበቅ፣ ለወንጀለኞች መደበቂያ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች በማጽዳትና የሥጋት ቦታዎችን ለይቶ መከላከል እንዲቻል የሠላም ሠራዊት አደረጃጀቶችን እና የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ሕዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ተችሏል።

👉የወንጀል ድርጊቶችን በመቀነስ ረገድ ከ3,628 በላይ የፀጥታ መረጃዎችና ጥቆማዎች በመሰብሰብና በማደራጀት ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሃሰተኛ ሰነድ፣ከከባድና ቀላል ወንጀል፣ ከትምህርት ተቋማት ደህንነት፣ ለፀጥታና ደህንነት አስጊ ከሆኑ ሁኔታዎችና ግጭቶች እንዲሁም ከተለያዩ አዋኪ ድርጊቶች፤ ከኢኮኖሚ አሻጥርና ህገ ወጥ የንግድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ከሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት 11,517 የወንጀል ድርጊቶችና የፀጥታ ስጋቶችን የመለየት፣ የመከላከል እና እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።

Comments are closed.