የተቋም ግንባታና አገልግሎነት አሰጣጥ በተመለከተ
በተቋማት ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ከ2 ሽህ 147 በላይ የመንግስት ሰራተኞች በህጻናት ማቆያ ልጆቻቸውን እንዲከባከቡ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።
በተቋማት ከ185 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ካፍቴሪያዎችን በመገንባት እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ እንዲሁም ከ150 የሸማች ሱቆችን ወደ ስራ በማስገባት ሰራተኞ የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።
ከ21 ሽህ 046 የተገልጋይ ማረፊያ በማዘጋጀት ምቹ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተዋል።
በተቋማት 347 አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ብልሹ አሰራር፣የተገልጋይ እንግልትና ምልልስ በማስቀረት የሚቀርቡ ቅሬታዎች እንዲቀንሱ አድርጓል።
በሌብነትና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ የገቡ 4 ሽህ 965 አመራሮች፣ ፈጻሚዎች እና ተገልጋዩችን ተጠያቂ በማድረግ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዷል።
