ቀዳማይ ልጅነትን ልማት ፕሮግራምን በተመለከተ
ፐሮግራሙ የከተማችንን 1.3 ሚሊዮን ህጻናትን በተለይ ደግሞ 330‚000 አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰብ የተገኙ ህጻናት ለመድረስ ያለሙ አምስት አንኳር ኢኒሼቲቮሽን አቅደን ስንተገብር ቆይተናል።
ከተቀመጡት ግቦች አንጻር የወላጆችን እና አሳዳጊዎች የምክር እና የሙያ አገልግሎት የሚሰጡ 5‚000 ሰራተኞችን በማሰማራት በ 4‚979 የመኖሪያ ብሎኮች ለሚገኙ ለ 487,544 ወላጆች/አሳዳጊዎች በየአስራ አምስት ቀኑ የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት ተሰጥቷል።
ለ11,900 አነስተኛ ገቢ ላላቸው እና ለድገት ውስኑነት ተጋላጭ የሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ከ 3 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ በየወሩ ተሰጥቷል።
ስራውን አጠናክሮ ለመቀጠል በዚህ በጀት አመትም ከ 5ዐዐ ሚሊየን በላይ በጀት ለአልሚ ምግብ በጅተናል፡፡
እድሜያቸው ከ 0 እስከ 3 ዓመት የሆኑ እና በኢኮኖሚ ሁኔታቸው ለዕድገት ውሱንነት ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት የዕድገት ሁኔታ ፕሮግራሙ በተጀመረበት ወቅት ከነበረበት 66.9% ወደ 73.1% በማደግ የ 6.2 በመቶ መሻሻል አሳይቷል።
በጨዋታ መልክ በማስተማር በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይታይ የነበረው የትምህርት ዝግጁነት ምጣኔም ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ ወደ 89.03% ከፍ በማለት የልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ችለናል፡፡
