የፍትህ ሥርዓትና የሕግ የበላይነትን ማስከበር በተመለከተ
በፍትህ ሥርዓታችን የሕግ የበላይነትን በማስከበር የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲጎለብት ለማድረግ በፍትሐብሔር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ክርክር በፍ/ቤት የመርታት አቅም 96.05 % ማድረስ ታቅዶ በፍርድ ቤት ክርክር የቀረቡ 6,379 መዝገቦች፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ካገኙ 3,963 መዝገቦች 3,683 ለአስተዳደሩ ማስወሰን በመቻሉ አፈፃፀሙ 96.8% ደርሷል፡፡
የመንግስት እና ሕዝብ መብትና ጥቅም በማስከበርም በገንዘብ 5,608,175,281.16 ብር ሆኖ በአይነት ደግሞ 272 ቤቶች፣ 64 ሼዶች እንዲሁም 260.32 ሄክታር መሬት ማስከበር መቻሉ፤ምርመራ ከተጠናቀቀ 12,828 የግል አቤቱታ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች ውስጥ 88% በእርቅ ለመጨረስ ታቅዶ 9,822 መዛግብት በፖሊስና በዐቃብያን ሕግ፣ 1,048 መዛግብት በፍርድ ቤት በአጠቃላይ 10,870 ክንውኑ 84.7% ሲሆን አፈፃፀሙ 96.2% ነው፡፡
