መስራት ያስከብራል፤ ውጤት ማስመዝገብም ያሸልማል!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች በ2017 በጀት ዓመት ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት የምስጋና እና የደረጃ እድገት አድርጎላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከ2009 ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያ ተደርጐላቸዉ የማያዉቅ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ እና በ2017 በጀት አመት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታው መስክ ለተገኘው ስኬት ለሰራተኞቹ የምስጋና እና እድገት የመስጠት መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በተካሄደው መርሃ ግብር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የደረጃ እድገት እና የደሞዝ ማሻሻያ በከተማ አስተዳደሩ ጸድቆ ይፋ ተደርጓል፡፡
“መስራት ያስከብራል ፤ውጤት ማስመዝገብም ያሸልማል!” ያሉት ከንቲባ አዳነች በሌላ በኩል ብክነት እና ሌብነትን በመከላከል በታማኝነት እና በትጋት መዲናችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ 24/7 እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የተሰጣችሁ እውቅና ይበልጥ ሰርታችሁ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሞራል ሆኗችሁ ከቀድሞው በላይ ጥራትን በመጨመር ፣ ብክነትን በማስወገድ እና ፍጥነትን በማሳደግ ልትሰሩ ይገባል ሲሉም የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
