+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደው የመንገድ ጥገና ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች የሚያደርገው ሁለገብ የመንገድ ጥገና ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ፍሰትን በማያስተጓጉል መልኩ በእረፍት ቀናትና በለሊት ክፍለ ጊዜ የአስፋልት መንገዶች የጥገና ስራዎችን በማከናወን የከተማዋን የትራፊት ፍሰት ምቹ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ባሳለፍነው ሳምንት የመንገድ ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከወንጌላዊት ህንፃ በጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ የሚወስደው መንገድ ይገኝበታል፡፡ መንገዱ አሁን ላይ ደረጃውን የጠበቀ የጥገና ስራ ተከናውኖለት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ በቀን ውስጥ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግደው የጐተራ ማሳለጫ መንገድ የተጐዳውን አፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት 310 ሜትር ርዝመት በ6 ሜትር የጐን ስፋት የአስፋልት እና የድሬኔጅ መስመርን ጨምሮ በመልሶ ግንባታ ደረጃ ጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡ ይህ የመንገድ ጥገና ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከወሎ ሠፈር ወደ ሳሪስ አቅጣጫ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ምቹ እንቅስቃሴ እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ በመንገዱ መጐዳት ምክንያት በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀንስ ይሆናል፡፡

2 Responses to “በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደው የመንገድ ጥገና ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

  • The focus of this study was on the ER HER2 subgroup, and because of the incomplete estimations of Ki67 and PR, we were not able to distinguish between Luminal A and B like tumours priligy side effects Third, our intervention was supervised by exercise trainers; however, community based exercise programs are increasingly available, such as LIVESTRONG at the YMCA, which offers free exercise programs to cancer survivors at various YMCA locations across the United States

  • cialis and priligy Anticancer Drugs 2010; 21 932 44

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *