+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመንገድ ዳር የውሃ መተላለፊያ መስመሮች እየተጠገኑ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመዲናችን የተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተጎዱና በቆሻሻ የተዘጉ የውሃ መፋሰሻ መስመሮችን የመጠገንና የማፅዳት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ባለስልጣኑ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ለዝናብ ውሃ መውረጃ አገልግሎት በተገነቡ የድሬኔጅ መስመሮች ውስጥ በሚጣሉ ጠጣር ነገሮች ምክንያት የከተማዋ የመንገድ ዳር ውሃ መፍሰሻ መስመሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዱና በክረምት ወራት ለጎርፍ አደጋ እያገለጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለችግሩ ከወዲሁ እልባት ለመስጠት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የድሬኔጅ መስመር ጥገና ሥራ በስፋት እየተከናወነ ነው፡፡አሁን ላይ ከልደታ መናፈሻ – 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ ከሆላንድ ኤምባሲ – ቀራንዮ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ – ጐጃም በረንዳ፣ ከጊዮርጊስ አደባባይ – አፍንጮ በር፣ ከደጐል አደባባይ – አቡነ ጴጥሮስ፣ ከአበቤ ሱቅ – ኮተቤ ኪዳነምህረት፣ አያት ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ፣ ሲ.ኤም.ሲ ፀሀይ ሪልስቴት፣ ላምበረት አቢሲኒያ ሆቴል አካባቢ፣ ከጉርድሾላ ወደ መገናኛ የሚወስዱ መንገዶች የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች የጥገናና የጽዳት ስራ እየተከናወነላቸው ይገኛል፡፡በቀጣይም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የድሬኔጅ መስመሮችን በመለየት የጥገናና የጽዳት ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንዲውሉ በማድረግ በኩል የከተማችን ነዋሪዎች አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያደርጉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *