+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቋሚ ኮሚቴው የባለሥልጣኑን የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም መገመገመ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱን 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ስራዎች የሚያሳይ ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድ በጀት እና ስትራቴጅክ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አብነት ኤርገንዶ፤ ተቋሙ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 497 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች በማከናወን ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ግዛቸው አይካ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ የግንባታና የጥገና ስራዎች አፈፃፀምና የተመሩበት አግባብ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።

ዶክተር ግዛቸው አክለውም ከተማዋ አሁንም ከሚያስፈልጋት የመንገድ ልማት ፍላጎት አንፃር ሰፊ ስራዎችን መስራት የሚጠይቅ በመሆኑ በባለስልጣኑ ያለውን ውጤታማ የስራ አፈፃፀም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረው፣ ቋሚ ኮሚቴው የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሰጡት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ ለመንገድ መሰረተ ልማት ማነቆ የሆኑ የወሰን ማስከበር እና ሌሎች እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች በመፍታት በኩል የቋሚ ኮሚቴው እገዛ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይም ልዩ ድጋፍ በሚፈልጉ ፕሮጀክቶች ላይ የድጋፍና ክትትል ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በቀጣዮቹ ቀናትም የአውቶቢስ ተራ – 18 ማዞሪያ፣ የአየር ጤና – ወለቴ እና የአቃቂ ቃሊቲ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በመስክ ተዘዋውሮ በመመልከት የማጠቃለያ ግብረ-መልስ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.