ለብልሽት የተዳረጉ አጫጭርና አቋራጭ የአስፋልት መንገዶችን በመጠገን የተሻለ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እያከናወነ ከሚገኘው የመንገድ ጥገና ስራ ጎን ለጎን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ሊያቃልሉ የሚችሉ አቋራጭ መንገዶችን እየጠገነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ የመዲናዋን የትራፊክ ፍሰት ምቹ ለማድረግ የጥገና ስራውን በዋና ዋና የቀለበት መንገድ ላይ አጠናክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተጎዱ አጫጭርና አቋራጭ መንገዶችን በመለየት በመልሶ ግንባታ ደረጃ የጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት የጥገና ስራው እየተከናወነባቸው ከሚገኙ የከተማዋ አካባቢዎች መካከል ከፍላሚንጎ ልዑል ሰገድ ህንፃ የሚወስደው አቋራጭ መንገድ ተጠቃሽ ነው፡፡
የጥገና ስራው 150 ሜትር ርዝመት እና 7ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍነው የአስፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity